1 “ሕይወቴን እጅግ ጠላሁ፤ስለዚህም ማጒረምረሜን ያለ ገደብ እለቃለሁ፤በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ።
2 እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፤በምን ላይ እንዳልተስማማን ንገረኝ እንጂ አትፍረድብኝ።
3 የክፉዎችን ዕቅድ በደስታ እየተቀበልህ፣እኔን ግን ስታስጨንቀኝ፣የእጅህንም ሥራ ስታዋርድ ደስ ይልሃልን?
4 አንተ ዐይንህ የሥጋ ለባሽ ዐይን ነውን?ሟች የሆነ የሰው ልጅ እንደሚያይ ታያለህን?
5 ዘመንህ እንደ ሟች ሰው ዘመን ነውን?ወይስ ዓመታትህ እንደ ሰው ዓመታት ናቸውን?
6 ታዲያ፣ በደልን የምትፈላልግብኝ፣ኀጢአቴንም የምትከታተለው ለምንድን ነው?