10 ሰዎች በፌዝ አፋቸውን ከፈቱብኝ፤በንቀት ጒንጬን ጠፈጠፉኝ፤በአንድነትም በላዬ ተሰበሰቡ።
11 እግዚአብሔር ለክፉዎች አሳልፎ ሰጠኝ፤በጠማሞችም እጅ ጣለኝ።
12 በሰላም እኖር ነበር፤ እርሱ ግን ሰባበረኝ፤ዐንገቴን ይዞ አደቀቀኝ፤ማነጣጠሪያ ዒላማው አደረገኝ፤
13 የእርሱ ቀስተኞች ከበቡኝ፤ያለ ርኅራኄ ኵላሊቴን ይበጣጥሳል፤ሐሞቴን መሬት ላይ ያፈሳል።
14 ደጋግሞ ይቀጠቅጠኛል፤እንደ ጦረኛም ተንደርድሮ ይመጣብኛል።
15 “በቈዳዬ ላይ ማቅ ሰፍቻለሁ፤ክብሬን በዐፈር ውስጥ ቀብሬአለሁ።
16 ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀልቶአል፤ጨለማም በዐይኖቼ ቆብ ላይ ዐርፎአል፤