12 በሰላም እኖር ነበር፤ እርሱ ግን ሰባበረኝ፤ዐንገቴን ይዞ አደቀቀኝ፤ማነጣጠሪያ ዒላማው አደረገኝ፤
13 የእርሱ ቀስተኞች ከበቡኝ፤ያለ ርኅራኄ ኵላሊቴን ይበጣጥሳል፤ሐሞቴን መሬት ላይ ያፈሳል።
14 ደጋግሞ ይቀጠቅጠኛል፤እንደ ጦረኛም ተንደርድሮ ይመጣብኛል።
15 “በቈዳዬ ላይ ማቅ ሰፍቻለሁ፤ክብሬን በዐፈር ውስጥ ቀብሬአለሁ።
16 ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀልቶአል፤ጨለማም በዐይኖቼ ቆብ ላይ ዐርፎአል፤
17 ነገር ግን በእጄ ዐመፅ አይገኝም፤ጸሎቴም ንጹሕ ነው።
18 “ምድር ሆይ፤ ደሜን አትሸፍኚ፤ጩኸቴም ማረፊያ አያግኝ!