1 ኢዮብም እንዲህ ሲል ንግግሩን ቀጠለ፤
2 “ፍትሕ የነሣኝ ሕያው እግዚአብሔርን!ነፍሴንም መራራ ያደረጋት፣ ሁሉን ቻይ አምላክን!
3 በውስጤ የሕይወት እስትንፋስ፣በአፍንጫዬም ውስጥ የእግዚአብሔር መንፈስ እስካለ ድረስ፣
4 ከንፈሬ ኀጢአትን አትናገርም፤አንደበቴም ሽንገላ አይወጣውም።