18 ይልቁን ድኻ አደጉን ከታናሽነቴ ጀምሮ እንደ አባት አሳደግሁት፤መበለቲቱንም ከተወለድሁ ጀምሮ መንገድ መራኋት፤
19 በልብስ ዕጦት ሰው ሲጠፋ፣ወይም ዕርቃኑን ያልሸፈነ ድኻ አይቼ፣
20 በበጎቼ ጠጒር ስላሞቅሁት፣ልቡ ባርኮኝ ካልሆነ፣
21 በአደባባይ ተሰሚነት አለኝ ብዬ፣በድኻ አደጉ ላይ እጄን አንሥቼ ከሆነ፣
22 ትከሻዬ ከመጋጠሚያው ይነቀል፤ክንዴም ከመታጠፊያው ይሰበር፤
23 የእግዚአብሔርን ቍጣ በመፍራቴ፣እንዲህ ያሉ ነገሮች መፈጸም አልቻልሁም።
24 “ወርቅን ተስፋ አድርጌ፣ወይም ንጹሑን ወርቅ፣ ‘አንተ መታመኛዬ ነህ’ ብዬ ከሆነ፣