ኢዮብ 42:4-10 NASV

4 “ ‘ስማኝ፣ ልናገር እኔ እጠይቃለሁ፤አንተ ትመልስልኛለህ’ አልኸኝ።

5 ጆሮዬ ስለ አንተ ሰምታ ነበር፤አሁን ግን ዐይኔ አየችህ።

6 ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፤በትቢያና በዐመድ ላይ ተቀምጬ ንስሓ እገባለሁ።”

7 እግዚአብሔር ይህን ለኢዮብ ከተናገረ በኋላ፣ ቴማናዊውን ኤልፋዝን እንዲህ አለው፤ “እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ስለ እኔ ቅን ነገር ስላልተናገራችሁ፣ ቍጣዬ በአንተና በሁለቱ ባልንጀሮችህ ላይ ነዶአል።

8 አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችና ሰባት አውራ በጎች ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም ስለ ራሳችሁ አቅርቡ። እንደ አሳፋሪ ተግባራችሁ እንዳላደ ርግባችሁ አገልጋዬ ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል፤ እኔም ጸሎቱን እቀበላለሁ፤ እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ስለ እኔ ቅን ነገር አልተናገራችሁምና።”

9 ቴማናዊው ኤልፋዝ፣ ሹሐዊው በልዳዶስና ናዕማታዊው ሶፋር እግዚአብሔር እንደ ተናገራቸው አደረጉ፤ እግዚአብሔርም የኢዮብን ጸሎት ተቀበለ።

10 ኢዮብ ለወዳጆቹ ከጸለየ በኋላ፣ እግዚአብሔር እንደ ገና አበለጸገው፤ ቀድሞ በነበረው ፈንታ ዕጥፍ አድርጎ ሰጠው።