24 ድንኳንህ በሚያስተማምን ሁኔታ እንዳለ ታውቃለህ፤በረትህን ትቃኛለህ፤ አንዳችም አይጐድልብህም።
25 ዘሮችህ አያሌ እንደሚሆኑ፣የምትወልዳቸውም እንደ ሣር እንደሚበዙ ታውቃለህ።
26 የእህል ነዶ ጐምርቶ በወቅቱ እንደሚሰበሰብ፣ዕድሜ ጠግበህ ወደ መቃብር ትሄዳለህ።
27 “እነሆ፤ ይህን ሁሉ መርምረናል፤ እውነት ሆኖ አግኝተነዋል፤ስለዚህ ልብ በል፤ ተቀበለውም።”