18 በየማለዳው ትመረምረዋለህ፤በየጊዜውም ትፈትነዋለህ።
19 ዐይንህን ከእኔ ላይ አታነሣምን?ምራቄን እንኳ እስክውጥ ፋታ አትሰጠኝምን?
20 ሰውን የምትከታተል ሆይ፤ኀጢአት ብሠራ፣ አንተን ምን አደርግሃለሁ?ለምን ዒላማህ አደረግኸኝ?ለምንስ ሸክም ሆንሁብህ?
21 መተላለፌን ለምን ይቅር አትልም?ኀጢአቴንስ ለምን አታስወግድልኝም?ትቢያ ውስጥ የምጋደምበት ጊዜ ደርሶአል፤ትፈልገኛለህ፤ እኔ ግን የለሁም።”