5 አካሌ ቈስሎ ትልና ቅርፊት ለብሶአል፤ቈዳዬ አፈክፍኮአል፤ ቍስሌም አመርቅዞአል።
6 “ዘመኔ ከሸማኔ መወርወሪያ ይልቅ ይፈጥናል፤ያለ ተስፋም ያልቃል።
7 ሕይወቴ ትንፋሽ ያህል እንደሆነች አስብ፤ዐይኔም ከእንግዲህ ደስታን አያይም።
8 አሁን የሚያየኝ ሰው ዐይን ከእንግዲህ አያየኝም፤ትፈልገኛለህ፤ እኔ ግን የለሁም።
9 ደመና በኖ እንደሚጠፋ፣ወደ መቃብር የሚወርድም አይመለስም።
10 ወደ ቤቱ ዳግመኛ አይመለስም፤ስፍራውም ከእንግዲህ አያውቀውም።
11 “ስለዚህ ከቶ ዝም አልልም፤በመንፈሴ ጭንቀት እናገራለሁ፤በነፍሴም ምሬት አጒረመርማለሁ።