9 ደመና በኖ እንደሚጠፋ፣ወደ መቃብር የሚወርድም አይመለስም።
10 ወደ ቤቱ ዳግመኛ አይመለስም፤ስፍራውም ከእንግዲህ አያውቀውም።
11 “ስለዚህ ከቶ ዝም አልልም፤በመንፈሴ ጭንቀት እናገራለሁ፤በነፍሴም ምሬት አጒረመርማለሁ።
12 በላዬ ጠባቂ ታደርግ ዘንድ፣እኔ ባሕር ነኝን ወይስ የባሕር አውሬ?
13 አልጋዬ ያጽናናኛል፣መኝታዬም ማጒረምረሜን ይቀንስልኛል ባልሁ ጊዜ፣
14 አንተ በሕልም ታስፈራራኛለህ፤በራእይም ታስደነግጠኛለህ፤
15 ስለዚህ እንዲህ ሆኖ ከመኖር፣መታነቅና መሞትን እመርጣለሁ።