10 ነገር ግን በባሕሮችና በወንዞች ውስጥ ከሚኖሩት ፍጡሮች ሁሉ፣ ከሚንፏ ቀቁት ወይም በውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ሕይወት ካላቸው ሌሎች ፍጡሮች መካከል ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው በእናንተ ዘንድ አስጸያፊዎች ይሁኑ፤
11 በእናንተ ዘንድ አስጸያፊ ስለሆኑ ሥጋቸውን አትብሉ፤ በድናቸውንም ትጸየፋላችሁ፤
12 ክንፍና ቅርፊት የሌለው ማንኛውም በውሃ ውስጥ የሚኖር ፍጡር በእናንተ ዘንድ አስጸያፊ ይሁን።
13 “ ‘ከአዕዋፍ ወገን እነዚህን ትጸየፋላችሁ፤ ጸያፍ ስለ ሆኑም አትብሏቸው፦ ንስር፣ ጥንብ አንሣ፣ ግልገል አንሣ፣
14 ጭላት፣ ማንኛውም ዐይነት ጭልፊት፣
15 ማንኛውም ዐይነት ቊራ፣
16 ሰጐን፣ ጠላቋ፣ ዝይ፣ ማንኛውም ዐይነት በቋል፣