15 ማንኛውም ዐይነት ቊራ፣
16 ሰጐን፣ ጠላቋ፣ ዝይ፣ ማንኛውም ዐይነት በቋል፣
17 ጒጒት፣ ርኩም፣ ጋጋኖ፣
18 የውሃ ዶሮ፣ ይብራ፣ ስደተኛ አሞራ፣
19 ሽመላ፣ ማንኛውም ዐይነት ሳቢሳ፣ ጅንጁላቴ ወፍና የሌሊት ወፍ።
20 “ ‘ክንፍ ኖሮአቸው በአራት እግር የሚንቀሳቀሱ ነፍሳት ሁሉ በእናንተ ዘንድ አስጸያፊዎች ይሁኑ።
21 ነገር ግን ክንፍ ኖሮአቸው በአራት እግር ከሚንቀሳቀሱ ነፍሳት መካከል ከምድር በሚፈናጠሩበት እግራቸው አንጓ ያለባቸውን መብላት ትችላላችሁ።