17 ጒጒት፣ ርኩም፣ ጋጋኖ፣
18 የውሃ ዶሮ፣ ይብራ፣ ስደተኛ አሞራ፣
19 ሽመላ፣ ማንኛውም ዐይነት ሳቢሳ፣ ጅንጁላቴ ወፍና የሌሊት ወፍ።
20 “ ‘ክንፍ ኖሮአቸው በአራት እግር የሚንቀሳቀሱ ነፍሳት ሁሉ በእናንተ ዘንድ አስጸያፊዎች ይሁኑ።
21 ነገር ግን ክንፍ ኖሮአቸው በአራት እግር ከሚንቀሳቀሱ ነፍሳት መካከል ከምድር በሚፈናጠሩበት እግራቸው አንጓ ያለባቸውን መብላት ትችላላችሁ።
22 ከእነዚህ ማንኛውንም ዐይነት አንበጣ፣ ፌንጣና ኵብኵባ መብላት ትችላላችሁ።
23 ነገር ግን ክንፍ ኖሮአቸው በአራት እግር የሚንቀሳቀሱትን ፍጥረታት ተጸየፏቸው።