28 የእነዚህን በድን የሚያነሣ ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሆኖም እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እንስሳቱም በእናንተ ዘንድ ርኵሳን ናቸው።
29 “ ‘ምድር ለምድር ከሚንቀሳቀሱ እንስሳት መካከል እነዚህ በእናንተ ዘንድ ርኩሳን ናቸው፦ ሙጭልጭላ፣ ዐይጥ፣ እንሽላሊት በየወገኑ፣
30 ዔሊ፣ ዐዞ፣ ገበሎ፣ አርጃኖ፣ ዕሥሥት።
31 ምድር ለምድር ከሚንቀሳቀሱ እንስሳት ሁሉ መካከል እነዚህ በእናንተ ዘንድ ርኩሳን ናቸው፤ ከእነዚህም የሞተውን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።
32 በድኑ በማንኛውም ዕቃ ላይ ቢወድቅ ያ ዕቃ ከዕንጨት፣ ከጨርቅ፣ ከቈዳ ወይም ከበርኖስ የተሠራ ቢሆን ርኩስ ይሆናል፤ በውሃ ውስጥ ይደረግ፤ ሆኖም ርኩስ ነው፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል።
33 በድኑም በሸክላ ዕቃ ውስጥ ቢወድቅ፣ በውስጡ ያለ ነገር ሁሉ ርኩስ ስለሚሆን ዕቃውን ስበሩት።
34 ማንኛውም ምግብ እንዲህ ካለው ዕቃ ውሃ ቢፈስበት ይረክሳል፤ ከዚህ ዕቃ የሚጠጣውም ነገር ሁሉ ርኵስ ነው፤