ዘሌዋውያን 17:4-10 NASV

4 በእግዚአብሔር (ያህዌ) ማደሪያ ፊት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባያመጣው፣ ያ ሰው በከንቱ ደም እንዳፈሰሰ ይቈጠራል፤ ደም በማፍሰሱም ከወገኖቹ ተለይቶ ይጥፋ።

5 እስራኤላውያን የሚሠዉትን መሥዋዕት ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) የሚያመጡበት ምክንያት ከዚሁ የተነሣ ነው። ይህንም ካህኑ ዘንድ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አምጥተው ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የኅብረት መሥዋዕት በማድረግ ያቅርቡ።

6 ካህኑም ደሙን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባለው በእግዚአብሔር (ያህዌ) መሠዊያ ላይ ይርጭ፤ ሥቡንም እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ ሽታ እንዲሆን ያቃጥል።

7 ከዚህ በፊት ላመነዘሩባቸው አጋንንት ከእንግዲህ ወዲህ ማንኛውንም መሥዋዕት ሊሠዉ አይገባም። ይህ ለእነርሱና ከእነርሱ በኋላ ለሚነሣው ትውልድ ሁሉ የዘላለም ሥርዐት ይሁን።’

8 “እንዲህም በላቸው፤ ‘የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት የሚያቀርብ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላቸው የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ፣

9 ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ባያቀርብ፣ ያ ሰው ከወገኖቹ ተለይቶ ይጥፋ።

10 “ ‘ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላቸው የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ ደም ቢበላ፣ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብድበታለሁ፤ ከወገኖቹም ለይቼ አጠፋዋለሁ፤