3 እንዲሁም ባለማግባቷ ከእርሱ ጋር ስለ ምትኖር እኅቱ ራሱን ሊያረክስ ይችላል።
4 ከእርሱ ጋር በጋብቻ ለሚዛመዱት ግን ራሱን አያርክስ።
5 “ ‘ካህናት ዐናታቸውን አይላጩ፤ የጢማቸውን ዙሪያ አይላጩ፤ ሰውነታቸውንም አይንጩ፤
6 ለአምላካቸው (ኤሎሂም) የተቀደሱ ይሁኑ፤ የአምላካቸውንም (ኤሎሂም) ስም አያርክሱ። ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቀርበውን መሥዋዕት የአምላካቸውን (ኤሎሂም) ምግብ ስለሚያቀርቡ ቅዱሳን ይሁኑ።
7 “ ‘ካህናት በዝሙት የረከሱትንም ሆነ ከባሎቻቸው የተፋቱትን ሴቶች አያግቡ፤ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተቀደሱ ናቸውና።
8 የአምላክህን (ኤሎሂም) ምግብ የሚያቀርብ ነውና ቀድሰው፤ እኔ የምቀድሳችሁ እግዚአብሔር (ያህዌ) ቅዱስ ነኝና ቅዱስ ይሁንላችሁ።
9 “ ‘የካህን ሴት ልጅ ዝሙት አዳሪ ሆና ራሷን ብታረክስ፣ አባቷን ታዋርዳለች፤ በእሳት ትቃጠል።