ዘሌዋውያን 23:2-8 NASV

2 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ‘የተቀደሱ ጉባኤዎች ብላችሁ የምትዋጇቸው የተመረጡ የእግዚአብሔር (ያህዌ) በዓላት እነዚህ ናቸው፤

3 “ ‘ሥራ የምትሠሩበት ስድስት ቀን አላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ሰንበት፣ የተቀደሰ ጉባኤ ዕለት ነው። የእግዚአብሔር (ያህዌ) ሰንበት ስለ ሆነ፣ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ምንም ዐይነት ሥራ አትሥሩበት።

4 “ ‘የተመረጡ የእግዚአብሔር (ያህዌ) በዓላት ብላችሁ በተወሰኑላቸው ጊዜያት የምታውጇቸው የተቀደሱ ጉባኤዎች እነዚህ ናቸው፤

5 የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት የእግዚአብሔር (ያህዌ) ፋሲካ በዓል ይጀመራል።

6 በዚያው ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን የእግዚአብሔር (ያህዌ) የቂጣ በዓል ይጀመራል፤ ሰባት ቀንም ያለ እርሾ የተጋገረ ቂጣ ትበላላችሁ።

7 በመጀመሪያው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዕለት ተግባራችሁንም አታከናውኑ።

8 ሰባት ቀን በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) አቅርቡ፤ በሰባተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ በዚያ ዕለት የተለመደ ተግባራችሁን አታከናውኑ።’ ”