1 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን በሲና ተራራ ላይ እንዲህ አለው፤
2 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ወደምሰጣችሁ ምድር በምትገቡበት ጊዜ ምድሪቱ ራስዋ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ሰንበት ታክብር።
3 ስድስት ዓመት በዕርሻህ ላይ ዝራ፤ ስድስት ዓመት ወይንህን ግረዝ፤ ፍሬውንም ሰብስብ።
4 በሰባተኛው ዓመት ግን ምድሪቱ የዕረፍት ሰንበት ታድርግ፤ ይህም የእግዚአብሔር (ያህዌ) ሰንበት ነው። በዕርሻህ ላይ አትዝራ፤ ወይንህንም አትግረዝ።