43 ምድሪቱ እነርሱ ለቀዋት ስለ ሄዱ ባዶ ትቀራለች፤ እነርሱ በሌሉበት ጊዜም ባድማ ሆና በሰንበትዋ ትደሰታለች፤ ሕጌን በማቃለላቸውና ሥርዐቴን በመናቃቸው፣ የኀጢአታቸውን ቅጣት ይቀበላሉ።
44 በዚህ ሁሉ ግን ከእነርሱ ጋር የገባሁትን ኪዳኔን በማፍረስ፣ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ ፈጽሜ እስካጠፋቸው ድረስ አልተዋቸውም፤ አልጸየፋቸውምም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ።
45 ስለ እነርሱም ስል፣ አምላካቸው (ኤሎሂም) እሆን ዘንድ አሕዛብ እያዩ ከግብፅ ምድር ካወጣኋቸው አባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ኪዳን አስባለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ”
46 እግዚአብሔር (ያህዌ) በራሱና በእስራኤላውያን መካከል በሲና ተራራ ላይ በሙሴ በኩል ያቆማቸው ሥርዐቶች፣ ሕጎችና ደንቦች እነዚህ ናቸው።