19 ቆሬም እነርሱን በመቃወም ተከታዮቹን ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በሰበሰባቸው ጊዜ፣ የእግዚአብሔር (ያህዌ) ክብር ለመላው ማኅበር ተገለጠ።
20 እግዚአብሔርም (ያህዌ) ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤
21 “ሁሉንም በአንድ ጊዜ እንዳጠፋቸው እናንተ ከዚህ ማኅበር ተለዩ።”
22 ሙሴና አሮን ግን በግንባራቸው ተደፍተው፣ “የሰብአዊ ፍጡር ሁሉ መንፈስ አምላክ (ኤሎሂም) የሆንህ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ አንድ ሰው ኀጢአት በሠራ በመላው ማኅበር ላይ ትቈጣለህን?” ሲሉ ጮኹ።
23 ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤
24 “ማኅበሩን ‘ከቆሬ፣ ከዳታንና ከአቤሮን ድንኳኖች ራቁ’ በላቸው።”
25 ሙሴ ተነሥቶ ወደ ዳታንና አቤሮን ሄደ፤ የእስራኤልም ሽማግሌዎች ተከተሉት።