10 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ “የአሮን በትር ለዐመፀኞቹ ምልክት እንድትሆን መልሰህ በምስክሩ ፊት ለፊት አኑራት፤ እነርሱ እንዳይሞቱም በእኔ ላይ የሚያደርጉትን ማጒረምረም ይህ ይገታዋል” አለው።
11 ሙሴም ልክ እግዚአብሔር (ያህዌ) እንዳዘዘው አደረገ።
12 ከዚያም እስራኤላውያን ሙሴን እንዲህ አሉት፤ “እነሆ መሞታችን ነው! ጠፋን፤ ሁላችንም መጥፋታችን ነው!
13 ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) ማደሪያ የሚጠጋ እንኳ ማንኛውም ሰው ቢሆን ይሞታል፤ ሁላችንም ልንጠፋ ነው እንዴ?”