ዘኁልቍ 18:19-25 NASV

19 እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ከሚያቀርቡት ከተቀደሰ ቊርባን የሚለየው ሁሉ ለአንተ፣ ለወንድና ለሴት ልጆችህ መደበኛ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፤ ይህም በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ለአንተና ለዘሮችህ ዘላለማዊ የጨው ኪዳን ነው።”

20 እግዚአብሔር (ያህዌ) አሮንን እንዲህ አለው፤ “ከምድራቸው የምትካፈለው ርስት፣ ከእነርሱም የምታገኘው ድርሻ የለህም፤ በእስራኤላውያን መካከል ድርሻህና ርስትህ እኔ ነኝ።

21 “በመገናኛው ድንኳን በሚያገለግሉበት ጊዜ ለሚሠሩት ሥራ ደመወዝ እንዲሆናቸው ከእስራኤል የሚወጣውን ዐሥራት ሁሉ ለሌዋውያን ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ።

22 አድራጎቱ ኀጢአት ስለ ሆነ ሞት እንዳ ያስከትልባቸው ከእንግዲህ ወዲያ እስራኤላውያን ወደ መገናኛው ድንኳን አይጠጉ።

23 በመገናኛው ድንኳን የሚከናወነውን ሥራ የሚሠሩት ሌዋውያን ናቸው፤ በዚያም ለሚፈጸመው በደል ኀላፊነቱን ይሸከማሉ። ይህም ለሚመጡት ትውልዶች የዘላለም ሥርዐት ነው፤ ሌዋውያን በእስራኤላውያን መካከል ርስት አይሰጣቸውም።

24 በዚህ ፈንታም እስራኤላውያን መባ አድርገው ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የሚያቀርቡትን ዐሥራት ለሌዋውያን ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እኔም እነርሱን በተመለከተ፣ ‘በእስራኤላውያን መካከል ርስት አይኖራቸውም’ ያልኩት በዚሁ ምክንያት ነው።”

25 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤