ዘኁልቍ 21:24-30 NASV

24 እስራኤል ግን በሰይፍ መታው፤ ከአርኖን እስከ ያቦቅ ድረስ ያለውንም ምድሩን ወሰደበት፤ ይሁን እንጂ የአሞናውያን ወሰን የተመሸገ ስለ ነበር ከያቦቅ አላለፈም።

25 እስራኤልም ሐሴቦንና በአካባቢዋ ያሉትን መንደሮች ጨምሮ የአሞራውያንን ከተሞች በሙሉ በመያዝ እዚያው ተቀመጠ።

26 ሐሴቦን የቀድሞውን የሞዓብን ንጉሥ ወግቶ እስከ አርኖን ድረስ ያለውን ምድሩን የወሰደበት የአሞራውያን ንጉሥ የሴዎን ከተማ ነበረች።

27 እንግዲህ ባለቅኔዎች እንደዚህ ያሉት ለዚህ ነው፤“ወደ ሐሴቦን ኑ፣ እንደ ገና ትገንባ፤የሴዎንም ከተማ ተመልሳ ትሠራ፤

28 “እሳት ከሐሴቦን ወጣ፤ነበልባልም ከሴዎን ከተማ ተንቦገቦገ፤የሞዓብን ዔር፣በአርኖን ከፍታዎች የሚኖሩትንም በላ።

29 ሞዓብ ሆይ፤ ወዮልህ!የከሞስ ሕዝብ ሆይ፤ ተደመሰስህ!ወንዶች ልጆቹን ለሽሽት፣ሴቶች ልጆቹን ለምርኮ፣ለአሞራውያን ንጉሥ ለሴዎን አሳልፎ ሰጥቶአል።

30 “እኛ ግን ገለበጥናቸው፤ሐሴቦን እስከ ዴቦን ድረስ ተደመሰሰች፤እስከ ኖፋ ድረስ ያሉትን፣እስከ ሜድባ የተዘረጉትን እንዳሉ አፈራርሰናቸዋል።”