62 አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሌዋውያን ወንዶች ሁሉ ተቈጥረው ሃያ ሦስት ሺህ ሆኑ፤ እነርሱም ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋር ርስት ተካፋዮች ስላልነበሩ አብረዋቸው አልተቈጠሩም።
63 ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ካለው ከሞዓብ ሜዳ ላይ የእስራኤልን ሕዝብ በቈጠሩበት ወቅት የተቈጠሩት እነዚህ ናቸው።
64 ሙሴና ካህኑ አሮን በሲና ምድረ በዳ እስራኤላውያንን በቈጠሩ ጊዜ ከእነዚህ ከተቈጠሩት መካከል አንዳቸውም አልነበሩም፤
65 ምክንያቱም በእርግጥ በምድረ በዳ እንደሚሞቱ ያን ጊዜ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነግሮአቸው ነበር፣ ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር ከእነርሱ የተረፈ ማንም ሰው አልነበረም።