4 ታዲያ አባታችን ወንድ ልጅ ባለመውለዱ ስሙ ከጐሣዎቹ ተለይቶ እንዴት ይጠፋል? ለእኛም በአባታችን ዘመዶች መካከል ርስት ስጡን።”
5 ስለዚህ ሙሴ ጒዳያቸውን ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) አቀረበ፤
6 እግዚአብሔርም (ያህዌ) እንዲህ አለው፤
7 “የሰለጰዓድ ልጆች ጥያቄ ትክክል ነው፤ በእርግጥ በአባታቸው ዘመዶች መካከል ድርሻቸውን ርስት አድርገህ ልትሰጣቸው ስለሚገባ የአባታቸውን ድርሻ ለእነርሱ አስተላልፍላቸው።
8 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘አንድ ሰው ወንድ ልጅ ሳይተካ ቢሞት ውርሱን ለሴት ልጁ አስተላልፉ።
9 ሴት ልጅ ከሌለችው ደግሞ ውርሱን ለወንድሞቹ ስጡ።
10 ወንድሞች ከሌሉትም ውርሱን ለአባቱ ወንድሞች ስጡ።