4 ከእያንዳንዱም የእስራኤል ነገድ አንዳንድ ሺህ ሰው ለጦርነቱ ላኩ።”
5 ስለዚህ ከእስራኤል ጐሣዎች ተወጣጥቶ ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ ሺህ በአጠቃላይ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰው ለጦርነት ተዘጋጀ።
6 ሙሴም የቤተ መቅደሱን ንዋየ ቅዱሳትና ምልክት መስጫ የሆኑትን መለከቶች ከያዘው ከካህኑ ከአልዓዛር ልጅ ከፊንሐስ ጋር ከየነገዱ አንዳንድ ሺህ ሰው ለጦርነት ላከ።
7 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከምድያም ጋር ተዋጉ፤ ወንዱንም በሙሉ ፈጁት፤
8 ከተገደሉትም መካከል አምስቱ የምድያም ነገሥታት ኤዊ፣ ሮቆም፣ ሱር፣ ሑርና ሪባ ይገኙባቸዋል፤ የቢዖርን ልጅ በለዓምንም በሰይፍ ገደሉት።
9 ከዚያም እስራኤላውያን የምድያማውያን ሴቶችና ሕፃናት ማረኩ፤ የቀንድ ከብቶቻቸውን፣ የበግና የፍየል መንጋዎቻቸውን ሁሉ ነዱ፤ ሀብታቸውንም በሙሉ ወሰዱ።
10 ምድያማውያኑ የሚኖሩባቸውን ከተሞች ሁሉ ሰፈሮቻቸውንም በሙሉ አቃጠሉ።