37 ይህ ከቀዓት ጐሣዎች ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ያገለገሉት ሰዎች ጠቅላላ ድምር ነው። ሙሴና አሮን፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እነዚህን ቈጠሯቸው።
38 ጌድሶናውያን በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው ተቈጥረው ነበር።
39 በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ለማገልገል የሚመጡት ከሠላሳ እስከ ሃምሳ ዓመት የሆናቸው ወንዶች ሁሉ፣
40 በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው የተቈጠሩት ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ሠላሣ ነበሩ።
41 ይህ ከጌድሶን ጐሣዎች በመገናኛው ድንኳን ያገለገሉት ሰዎች ጠቅላላ ድምር ነው፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ሙሴና አሮን እነዚህን ቈጠሯቸው።
42 ሜራሪያውያንም በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው ተቈጥረው ነበር።
43 በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ለማገልገል የሚመጡት ከሠላሳ እስከ አምሳ ዓመት የሆናቸው ወንዶች ሁሉ፣