1 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤
2 “ተላላፊ የቆዳ በሽታ ያለበትን ወይም ማንኛውም ዐይነት ፈሳሽ ከሰውነቱ የሚወጣውን ወይም ሬሳ በመንካቱ በሥርዐቱ መሠረት የረከሰውን ሰው ሁሉ ከሰፈር እንዲያስወጡ እስራኤላውያንን እዘዝ፤
3 ወንድም ሆነ ሴት አስወጡ፤ እኔ በመካከላቸው የምኖርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ ከሰፈር አስወጧቸው።”
4 እስራኤላውያን ይህንኑ አደረጉ፤ ሰዎቹንም ከሰፈር አስወጧቸው፤ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘውም መሠረት ፈጸሙ።
5 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤
6 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘ወንድም ሆነ ሴት በማናቸውም ረገድ ሌላውን ቢበድልና ከዚህም የተነሣ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ዘንድ ያለውን ታማኝነት ቢያጐድል ያ ሰው በደለኛ ነው