40 ከመጀመሪያው የበግ ጠቦት ጋር የኢፍ መስፈሪያ አንድ ዐሥረኛ ምርጥ ዱቄትን ተወቅጦ ከተጠለለ ሩብ ኢፍ ዘይት ጋር ለውስና ሩብ ኢን ወይንን ደግሞ የመጠጥ መሥዋዕት በማድረግ አቅርብ።
41 ሌላውን የበግ ጠቦት በማለዳው እንደ ቀረበው ተመሳሳይ ከሆነው የእህልና የመጠጥ መሥዋዕት ጋር በምሽት ሠዋው፤ ይህም ጣፋጭ መዓዛና ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ነው።
42 “ይህ የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ በሚመጡት ትውልዶች ዘወትር ይደረጋል፤ በዚያ እገናኝሃለሁ፤ እናገርሃለሁም፤
43 በዚያ ደግሞ ከእስራኤላውያን ጋር እገናኛለሁ፤ ስፍራውም በክብሬ ይቀደሳል።
44 “ስለዚህ የመገናኛው ድንኳንና መሠዊያውን እኔ እቀድሳለሁ፤ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ አሮንና ወንድ ልጆቹን እቀድሳለሁ።
45 ከዚያም በእስራኤላውያን መካከል እኖራለሁ፤ አምላካቸውም (ኤሎሂም) እሆናለሁ።
46 በመካከላቸውም እኖር ዘንድ ከግብፅ ያወጣኋቸው እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር (ያህዌ) መሆኔን ያውቃሉ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) አምላካቸው ነኝ።