21 “ልጁም፣ ‘አባቴ ሆይ፤ በሰማይና በአንተ ፊት በድያለሁ፤ ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም’ አለው።
22 “አባቱ ግን አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፤ ‘ፈጥናችሁ ከሁሉ ምርጥ የሆነውን ልብስ አምጡና አልብሱት፤ ለጣቱቀለበት፣ ለእግሩም ጫማ አድርጉለት፤
23 የሰባውንም ፍሪዳ አምጡና ዕረዱ፤ እንብላ፤ እንደሰት፤
24 ይህ ልጄ ሞቶ ነበር፤ አሁን ግን ሕያው ሆኖአል፤ ጠፍቶም ነበር፤ ተገኝቶአል።” ከዚያም ይደሰቱ ጀመር።
25 “በዚህ ጊዜ ታላቁ ልጅ በዕርሻ ቦታ ነበረ፤ ከዚያም ተመልሶ ወደ ቤት በተቃረበ ጊዜ፣ የሙዚቃና የጭፈራ ድምፅ ሰማ፤
26 እርሱም ከአገልጋዮቹ አንዱን ጠርቶ ነገሩ ምን እንደሆነ ጠየቀው።
27 አገልጋዩም፣ ‘ወንድምህ መጥቶአል፤ በሰላም በጤና ስለ መጣም አባትህ የሰባውን ፍሪዳ ዐርዶለታል’ አለው።