2 ሳሙኤል 23:1-7 NASV

1 የዳዊት የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው፤“በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፣ልዑል ከፍ ከፍ ያደረገው ሰው፣የእስራኤል ተወዳጁ ዘማሪ፣የእሴይ ልጅ የዳዊት የትንቢት ቃል ይህ ነው፤

2 “የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ተናገረ፤ቃሉ በአንደበቴ ላይ ነበረ።

3 የእስራኤል አምላክ ተናገረ፤የእስራኤልም ዐለት እንዲህ አለኝ፤ሰዎችን በጽድቅ የሚገዛ፣በፈሪሀ እግዚአብሔርም የሚያስተዳድር፣

4 እርሱ፣ ደመና በሌለበት፣ በማለዳ ፀሓይ በምትወጣበት ጊዜ፣እንዳለው ብርሃን ነው፤በምድር ላይ ሣርን እንደሚያበቅለው፣ከዝናብም በኋላ እንዳለው የብርሃን ጸዳል ነው።’

5 “የእኔስ ቤት በእግዚአብሔር ዘንድ ትክክል አይደለምን?ሁሉንም ነገር አዘጋጅቶና ጠብቆ፣ከእኔ ጋር ዘላለማዊ ኪዳን ያደረገ አይደለምን?ድነቴን ከፍጻሜ የሚያደርሰው፣መሻቴን ሁሉ የሚሰጠኝ እርሱ አይደለምን?

6 ነገር ግን ክፉ ሰዎች ሁሉ፣በእጅ እንደማይሰበሰብ እንደ እሾኽ ይጣላሉ።

7 እሾኽ የሚነካ ሁሉ፣የብረት መሣሪያ ወይም የጦር ዘንግ ይይዛል፤ባሉበትም ቦታ ፈጽመው በእሳት ይቃጠላሉ።