2 ሳሙኤል 3:31-37 NASV

31 ከዚያም ዳዊት ለኢዮአብና አብሮት ለነበረው ሕዝብ ሁሉ፣ “ልብሳችሁን ቀዳችሁ፣ ማቅ ለብሳችሁ በአበኔር ፊት አልቅሱ” አላቸው፤ ራሱ ንጉሥ ዳዊትም አስከሬኑን አጀበ።

32 ከዚያም አበኔርን በኬብሮን ቀበሩት፤ ንጉሡም በአበኔር መቃብር ላይ ጮኾ አለቀሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ እንደዚሁ አለቀሱ።

33 ንጉሡም ለአበኔር ይህን የሐዘን እንጒርጒሮ ተቀኘ፤“አበኔር እንደ ተራ ሰው ይሙት?

34 እጆችህ አልታሰሩም፤እግሮችህ በእግር ብረት አልገቡም፤ሰው በክፉ ሰዎች ፊት እንደሚወድቅአንተም እንደዚሁ ወደቅህ።”ሕዝቡም ሁሉ እንደ ገና አለቀሱለት።

35 ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እህል በሚቀምስበት ሰዓት ወደ ዳዊት መጥተው ምግብ እንዲበላ አጥብቀው ለመኑት። ዳዊት ግን፣ “ፀሓይ ከመጥለቋ በፊት እንጀራ ወይም ሌላ ነገር ብቀምስ፣ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ከዚህም የባሰ ያምጣብኝ” ብሎ ማለ።

36 ሕዝቡም ሁሉ ይህንኑ ተመለከቱ፤ ደስም አላቸው፤ በእርግጥ ንጉሡ ያደረገው ሁሉ ሕዝቡን ደስ አሰኛቸው።

37 እንዲሁም በዚያን ዕለት ሕዝቡ ሁሉና እስራኤል በሙሉ ንጉሡ በኔር ልጅ በአበኔር ሞት እጁ እንዳልገባበት ዐወቁ።