መሳፍንት 16:21-27 NASV

21 ከዚያም ፍልስጥኤማውያን ያዙት፤ ዐይኖቹን አውጥተው ወደ ጋዛ ይዘውት ወረዱ፤ በናስ ሰንሰለት አስረውም እስር ቤት ውስጥ እህል እንዲፈጭ አደረጉት፤

22 ነገር ግን ከተላጨ በኋላ ጠጒሩ እንደ ገና ማደግ ጀመረ።

23 በዚህ ጊዜ የፍልስጥኤማውያን ገዦች፣ “አምላካችን ዳጎን፣ ጠላታችን ሳምሶንን በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናል” ብለው በመደሰት ለአምላካቸው ለዳጎን ታላቅ መሥዋዕት ለማቅረብ ተሰበሰቡ።

24 ሕዝቡም ሳምሶንን ባዩት ጊዜ፣ አምላካቸውን ዳጎንን በማመስገን፣“ምድራችንን ያጠፋውን፣ብዙ ሰው የገደለብንን፣ ጠላታችንን፣አምላካችን በእጃችን አሳልፎ ሰጠን” አሉ።

25 እጅግ ደስ ባላቸው ጊዜ፣ “እንዲያዝናናን ሳምሶንን አምጡት” አሉ፤ ስለዚህ ሳምሶንን ከእስር ቤት ጠርተው አስመጡት፤ በፊታቸውም ተጫወተ።በምሶሶዎቹ መካከል ባቆሙት ጊዜ፣

26 ሳምሶን እጁን ይዞ የሚመራውን ልጅ፣ “ቤተ ጣዖቱ ደግፈው ወደ ያዙት ምሰሶዎች አስጠጋኝና ልደገፋቸው” አለው።

27 በዚህ ጊዜ ወንዶችና ሴቶች ቤተ ጣዖቱን ሞልተውት ነበር፤ የፍልስጥኤማውያን ገዦችም በሙሉ በዚያ ነበሩ፤ ሳምሶን ሲጫወት ለማየት ሦስት ሺህ ያህል ወንዶችና ሴቶች በጣራው ላይ ነበሩ።