ኢዮብ
ምዕራፎች 32:1-7
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
1ኢዮብ በበኩሉ ራሱን እንደ ጻድቅ ቈጥሮ ስለ ነበር፣ እነዚህ ሦስት ሰዎች ለእርሱ መልስ መስጠታቸውን ተዉ።
2ከራም ወገን የሆነው፣ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ግን ኢዮብ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን ጻድቅ ስላደረገ፣ እጅግ ተቈጣው።
3ሦስቱ የኢዮብ ጓደኞች በኢዮብ ላይ መፍረድ እንጂ፣ ነገሩን ሊያሳምኑት ስላልቻሉ፣ በእነርሱም ላይ ተቈጣ።
4ኤሊሁ፣ ሌሎቹ በዕድሜ ይበልጡት ስለ ነበር ከእነርሱ ቀድሞ ለኢዮብ ሳይናገር ቈየ።
5ነገር ግን እነዚህ ሦስቱ የሚሉትን ባጡ ጊዜ ቍጣው ነደደ።
6ስለዚህ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ እንዲህ አለ፤“እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፤እናንተ ግን አዛውንቶች ናችሁ፤ከዚህም የተነሣ የማውቀውን ለመናገር አልደፈርሁም፤ፈርቼ ዝም አልሁ።
7‘ዕድሜ ይናገራል፤ረጅም ዘመን ጥበብን ያስተምራል’ ብዬ ነበር።