10 “ስለዚህ፣ ‘ስሙኝ፣እኔም የማውቀውን ልንገራችሁ’ እላለሁ።
11 እናንተ በምትነጋገሩበት ጊዜ ታገሥሁ፤ቃላት እየመረጣችሁ ስትናገሩ፣በጥሞና ሰማኋችሁ፤
12 በሙሉ ልብ አዳመጥኋችሁ፤ነገር ግን ከእናንተ የኢዮብን ቃል ያስተባበለ ማንም የለም፤ለንግግሩም አጸፋ የመለሰ አልተገኘም።
13 ‘እኛ ጥበብ አግኝተናል፤ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ይርታው’ አትበሉ።
14 ኢዮብ ግን ቃሉን በእኔ ላይ አልሰነዘረም፤እኔም እንደ እናንተ አነጋገር መልስ አልሰጠውም።
15 “እነርሱ ተስፋ ቈርጠው፤ የሚሉት የላቸውም፤የሚናገሩትም ጠፍቶአቸዋል።
16 እንግዲህ እነርሱ መልስ ስላጡ፣ጸጥ ብለውም ስለ ቆሙ፣ በትዕግሥት ልጠብቅን?