12 እግዚአብሔርም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛውን የኢዮብን ሕይወት ባረከ። እርሱም ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፣ ስድስት ሺህ ግመሎች፣ አንድ ሺህ ጥማድ በሬዎች፣ አንድ ሺህ እንስት አህዮችም ነበሩት።
13 ደግሞም ሰባት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤
14 የመጀመሪያዋን ይሚማ፣ ሁለተኛዋን ቃሥያ፣ ሦስተኛዋንም አማልቶያስ ቂራስ ብሎ ሰየማቸው።
15 እንደ ኢዮብ ሴቶች ልጆች የተዋቡ ሴቶች በምድሪቱ ሁሉ አልተገኙም፤ አባታቸውም ከወንድሞቻቸው ጋር ርስት ሰጣቸው።
16 ከዚህ በኋላ ኢዮብ አንድ መቶ አርባ ዓመት ኖረ፤ ልጆቹንና የልጅ ልጆቹን እስከ አራት ትውልድ ድረስ አየ።
17 በዚህ ሁኔታ አርጅቶ፣ ዕድሜ ጠግቦ ሞተ።