ዘሌዋውያን 17:7-13 NASV

7 ከዚህ በፊት ላመነዘሩባቸው አጋንንት ከእንግዲህ ወዲህ ማንኛውንም መሥዋዕት ሊሠዉ አይገባም። ይህ ለእነርሱና ከእነርሱ በኋላ ለሚነሣው ትውልድ ሁሉ የዘላለም ሥርዐት ይሁን።’

8 “እንዲህም በላቸው፤ ‘የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት የሚያቀርብ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላቸው የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ፣

9 ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ባያቀርብ፣ ያ ሰው ከወገኖቹ ተለይቶ ይጥፋ።

10 “ ‘ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላቸው የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ ደም ቢበላ፣ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብድበታለሁ፤ ከወገኖቹም ለይቼ አጠፋዋለሁ፤

11 የፍጡር ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና፤ በመሠዊያ ላይ ለሕይወታችሁ ማስተስረያ እንዲሆን ደሙን ሰጥቻችኋለሁ፤ ለሰውም ሕይወት ስርየት የሚያስገኝ ደም ነው።

12 ስለዚህ እስራኤላውያንን፣ “ከእናንተ ማንም ደም አይብላ፤ በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛም ቢሆን ደም አይብላ” አልሁ።

13 “ ‘እንዲበላ የተፈቀደውን ማንኛውንም እንስሳ ወይም ወፍ አድኖ የያዘ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላችሁ የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ ደሙን ከውስጡ ያፍስስ፤ ዐፈርም ያልብሰው፤