ዘኁልቍ
ምዕራፎች 1:26-32
መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም
26ከይሁዳ ዝርያ፦ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።
27ከይሁዳ ነገድ የተቈጠሩትም ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበሩ።
28ከይሳኮር ዝርያ፦ዕድሜአቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።
29ከይሳኮር ነገድ የተቈጠሩትም አምሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።
30ከዛብሎን ዝርያ፦ዕድሜያቸው ሃያ አመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።
31ከዛብሎን ነገድ የተቈጠሩትም አምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።
32ከዮሴፍ ልጆች፦ከኤፍሬም ዝርያ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።