4 ወዲያው እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን፣ አሮንንና ማርያምን፣ “ሦስታችሁም ውጡና ወደ መገናኛው ድንኳን ኑ” አላቸው፤ ሦስቱም ወጥተው ሄዱ።
5 ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) በደመና ዐምድ ወረደ፤ በድንኳኑም ደጃፍ ቆሞ አሮንንና ማርያምን ጠራቸው፤ ሁለቱም ወደ እርሱ በቀረቡ ጊዜ፣
6 እንዲህ አላቸው፤ “ቃሌን አድምጡ፤“የእግዚአብሔር (ያህዌ) ነቢይ በመካከላችሁ ቢኖር፣በራእይ እገለጥለታለሁ፤በሕልምም እናገረዋለሁ።
7 ለአገልጋዬ ሙሴ ግን እንዲህ አይደለም፤እርሱ በቤቴ ሁሉ የታመነ ነው።
8 እኔ ከእርሱ ጋር የምነጋገረው ፊት ለፊት ነው፤በግልጽ እንጂ በልዩ ዘይቤ አይደለም፤እርሱ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) መልክ ያያል።ታዲያ እናንተ አገልጋዬን ሙሴንትቃወሙ ዘንድ ለምን አልፈራችሁም?”
9 የእግዚአብሔር (ያህዌ) ቍጣ በላያቸው ነደደ፤ እርሱም ትቶአቸው ሄደ።
10 ደመናው ከድንኳኑ ላይ በተነሣ ጊዜ፣ እነሆ፤ ማርያም በለምጽ ተመታች፤ እንደ በረዶም ነጣች። አሮንም ወደ እርሷ ዘወር ሲል ለምጽ ወርሶአት አየ፤