1 እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤
2 “እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘እንድትኖሩበት ወደምሰጣችሁ ምድር ከገባችሁ በኋላ፣
3 ስእለታችሁን ለመፈፀም ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ለማድረግ ወይም በተወሰኑ በዓሎቻችሁ ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ከላም ወይም ከበግ መንጋ በእሳት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ስታቀርቡ
4 መሥዋዕቱን ይዞ የሚመጣው ሰው በኢን አንድ አራተኛ ዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ የላመ ዱቄት የእህል ቊርባን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ያቀርባል።
5 ለሚቃጠል ወይም ለዕርድ መሥዋዕት ከሚቀርብ ከእያንዳንዱ የበግ ጠቦት ጋር የኢን አንድ አራተኛ የወይን ጠጅ የመጠጥ ቊርባን አብራችሁ አዘጋጁ።