ዘኁልቍ 15:3-9 NASV

3 ስእለታችሁን ለመፈፀም ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ለማድረግ ወይም በተወሰኑ በዓሎቻችሁ ሽታው እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ከላም ወይም ከበግ መንጋ በእሳት ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ስታቀርቡ

4 መሥዋዕቱን ይዞ የሚመጣው ሰው በኢን አንድ አራተኛ ዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ የላመ ዱቄት የእህል ቊርባን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ያቀርባል።

5 ለሚቃጠል ወይም ለዕርድ መሥዋዕት ከሚቀርብ ከእያንዳንዱ የበግ ጠቦት ጋር የኢን አንድ አራተኛ የወይን ጠጅ የመጠጥ ቊርባን አብራችሁ አዘጋጁ።

6 “ ‘ከአውራ በግ ጋር በኢን ሢሶ ዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ ልም ዱቄት የእህል ቍርባን አዘጋጁ፤

7 እንዲሁም ለመጠጥ ቊርባን የሚሆን የኢን አንድ ሦስተኛ የወይን ጠጅ አዘጋጁ፤ ይህንም እግዚአብሔርን (ያህዌ) ደስ የሚያሰኝ ሽታ ያለው አድርጋችሁ አቅርቡ።

8 “ ‘አንዱን ወይፈን ለተለየ ስለት ወይም ለኅብረት የሚቀርብ የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም የዕርድ መሥዋዕት አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) በምታዘጋጁበት ጊዜ፣

9 ከወይፈኑ ጋር በግማሽ ኢን ዘይት የተለወሰ የኢፍ ሦስት ዐሥረኛ የላመ ዱቄት አብራችሁ አምጡ።