3 በድል አድራጊነቴ ደስ የሚላቸውን ቅዱሳኔን አዛለሁ፤ቍጣዬንም እንዲፈጽሙ፣ተዋጊዎቼን ጠርቻለሁ።
4 በተራሮች ላይ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፣የሚሰማውን ጩኸት አድምጡበመንግሥታትም መካከል፣እንደ ተጨናነቀ ሕዝብ ድምፅ የሆነውን ውካታ ስሙ!የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርሰራዊቱን ለጦርነት አሰልፎአል።
5 እግዚአብሔርና የቍጣው ጦር መሣሪያ፣ምድሪቱን በሙሉ ለማጥፋት፣ከሩቅ አገር፣ከሰማያትም ዳርቻ መጥተዋል።
6 የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና አልቅሱ፤ሁሉን ቻይ ከሆነ አምላክ ዘንድ ጥፋት ይመጣልና።
7 ስለዚህ እጆች ሁሉ ሽባ ይሆናሉ፤የሰውም ሁሉ ልብ ይቀልጣል።
8 ሽብር ይይዛቸዋል፤ሥቃይና ጭንቀት ይደርስባቸዋል፤ምጥ እንደ ያዛት ሴት ያምጣሉ፤እርስ በርሳቸው በድንጋጤ ይተያያሉ፤ፊታቸውም በፍርሀት ቀይ ይሆናል።
9 እነሆ፤ የእግዚአብሔር ቀን ጨካኝ ነው፤ምድርን ባድማ ሊያደርጋት፣በውስጧም ያሉትን ኀጢአተኞች ሊያጠፋ፣ከመዓትና ከብርቱ ቍጣ ጋር ይመጣል።