ኢሳይያስ 35 NASV

የተቤዠ ሕዝብ ደስታ

1 ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፤በረሓው ሐሤት ያደርጋል፤ ይፈካል፤እንደ አደይም ያብባል።

2 በደስታና በዝማሬ ሐሤት ያደርጋል፤የሊባኖስ ክብር ይሰጠዋል፤የቀርሜሎስንና የሳሮንን ግርማ ይለብሳል።የአምላካችንን ታላቅ ግርማ፣ የእግዚአብሔርን ክብር ያያሉ።

3 የደከሙትን እጆች አበርቱ፤የላሉትንም ጒልበቶች አጽኑ፤

4 የሚፈራ ልብ ላላቸው እንዲህ በሉ፤“በርቱ፤ አትፍሩ፤አምላካችሁ ይመጣል፤ሊበቀል ይመጣል፤እርሱም ብድራቱን ይዞ፣ሊያድናችሁ ይመጣል።”

5 በዚያን ጊዜም የዕውር ዐይኖች ይገለጣሉ፤የደንቈሮም ጆሮዎች ይከፈታሉ።

6 አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘላል፤የድዳውም አንደበት በደስታ ይዘምራል፤ውሃ ከበረሓ ይወጣል፤ምንጮችም ከምድረ በዳ ይፈልቃሉ።

7 ንዳዳማው ምድር ኵሬ ይሆናል፤የተጠማው መሬት ውሃ ያመነጫል።ቀበሮዎች በተኙባቸው ጒድጓዶች፣ሣር፣ ሸምበቆና ደንገል ይበቅልበታል።

8 በዚያ አውራ ጐዳና ይሆናል፤“የተቀደሰ መንገድ” ተብሎ ይጠራል።የረከሱ አይሄዱበትም፤በመንገዱ ላይ ላሉት ብቻ ይሆናል።ገራገሮችም ከመንገዱ አይስቱም።

9 አንበሳ አይኖርበትም፤ነጣቂ አውሬም አይወጣበትም፤እነዚህማ በዚያ ስፍራ አይገኙም፤የዳኑት ብቻ በዚያ ይሄዳሉ፤

10 እግዚአብሔር የዋጃቸው ይመለሳሉ።እየዘመሩ ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ዘላለማዊ ደስታን እንደ አክሊል ይቀዳጁታል፤ፍሥሓና ሐሤት ያገኛሉ፤ሐዘንና ትካዜ ከዚያ ይሸሻሉ።

ምዕራፎች

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26 27 28 29 30 31 32 33 34 35 36 37 38 39 40 41 42 43 44 45 46 47 48 49 50 51 52 53 54 55 56 57 58 59 60 61 62 63 64 65 66