ኢሳይያስ 31 NASV

በግብጽ ለሚደገፉ ወዮውላቸው

1 ወደ እስራኤል ቅዱስ ለማይመለከቱ፣ ከእግዚአብሔርም ርዳታን ለማይሹ፣ነገር ግን፤ ለርዳታ ብለው ወደ ግብፅ ለሚወርዱ፣በፈረሶች ለሚታመኑ፣በሠረገሎቻቸው ብዛት፣በፈረሶቻቸውም ታላቅ ብርታት ለሚመኩ ወዮላቸው!

2 እርሱም ግን ጠቢብ ነው፤ ጥፋትን ያመጣል፤ቃሉን አያጥፍም።በክፉ አድራጊዎች ቤት ላይ፣በደለኞችንም በሚረዱ ላይ ይነሣል።

3 ግብፃውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ እግዚአብሔር እጁን ሲዘረጋ፣ርዳታ ሰጪው ይሰናከላል፤ተረጂውም ይወድቃል፤ሁለቱም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።

4 እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛል፤“አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦልየሰበረውን ይዞ ሲያገሣ፣ብዙ እረኞችተጠራርተው ሲመጡበት፣ጩኸታቸው እንደማያስፈራው፣በድምፃቸውም እንደማይታወክ፣የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣በጽዮን ተራራና በከፍታዎቿ ላይ ለውጊያ እንዲሁ ይወርዳል።

5 በዐናት ላይ እንደሚያንዣብቡ ወፎች፣የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን እንዲሁ ይጋርዳታል፤ይከልላታል፤ ይታደጋታል፤በላይዋ ያልፋል፤ ያድናታልም።”

6 እናንተ እስራኤላውያን ሆይ፤ እጅግ ወዳ መፃችሁበት ወደ እርሱ ተመለሱ።

7 በዚያን ቀን በኀጢአት የተሞላ እጃችሁ የሠራቸውን የወርቅና የብር ጣዖቶች ሁላችሁም ትጥላላችሁና።

8 “አሦር የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃል፤የሥጋ ለባሽ ያልሆነም ሰይፍ ይበላዋል።ከሰይፍ ፊት ይሸሻል፤ጐልማሶቹም የግዳጅ ሥራ ይሠራሉ።

9 ጠንካራ ምሽጉ በሽብር ምክንያት ይወድቃል፤መሪዎቹም የጦር ዐርማ ሲያዩበድንጋጤ ይዋጣሉ”ይላል እሳቱ በጽዮን፣ማንደጃውም በኢየሩሳሌም የሆነ እግዚአብሔር።

ምዕራፎች

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26 27 28 29 30 31 32 33 34 35 36 37 38 39 40 41 42 43 44 45 46 47 48 49 50 51 52 53 54 55 56 57 58 59 60 61 62 63 64 65 66