1 የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ይህ ነው፤
2 በዘመኑም ፍጻሜ፣ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተራራከተራሮች ከፍ ብሎ ይመሠረታል፤ከኰረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ሕዝቦችም ሁሉ ወደዚያ ይጐርፋሉ።
3 ብዙ ሕዝቦችም መጥተው እንዲህ ይላሉ፤“ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤በጐዳናውም እንሄዳለን።”ሕግ ከጽዮን፣ የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።
4 እርሱ በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤የብዙ ሰዎችን አለመግባባት ያስወግዳል።እነርሱም ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻጦራቸውንም ማጭድ ያደርጋሉ።ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ጦርነትንም ከእንግዲህ አይማሩም።
5 እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ ኑ፤ በእግዚአብሔር ብርሃን እንመላለስ።
6 የያዕቆብ ቤት የሆነውን፣ሕዝብህን ትተሃል፤እነርሱ በምሥራቅ ሰዎች ከንቱ አምልኮ ተሞልተዋልና፤እንደ ፍልስጥኤማውያን ያሟርታሉ፤ከባዕዳን ጋር አገና ይማታሉ።
7 ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፤ሀብታቸውም ልክ የለውም።ምድራቸው በፈረሶች ተሞልታለች፤የሠረገሎቻቸውም ብዛት ልክ የለውም።
8 ምድራቸው በጣዖታት ተሞልታለች፤ጣቶቻቸው ላበጇቸው፣ለእጆቻቸው ሥራ ይሰግዳሉ።
9 ሰው ዝቅ ብሎአል፤የሰው ልጅም ተዋርዶአል፤ስለዚህ በደላቸውን ይቅር አትበል።
10 ከእግዚአብሔር አስፈሪነት ከግርማው ሽሽ፤ወደ ዐለቶች ሂድ፤በመሬትም ውስጥ ተሸሸግ።
11 የእብሪተኛ ሰው ዐይን ይሰበራል፤የሰዎችም ትዕቢት ይዋረዳል፤በዚያን ቀን እግዚአብሔር ብቻውን ከፍ ከፍ ይላል።
12 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርእብሪተኛውንና ትዕቢተኛውን ሁሉ፣የተኵራራውን በሙሉየሚያዋርድበት ቀን አለው።
13 ረዥምና ከፍ ከፍ ያሉትን የሊባኖስ ዝግባዎች ሁሉ፣የባሳንን የወርካ ዛፎች ሁሉ፣
14 ታላላቁን ተራራ ሁሉ፣ከፍ ያለው ኰረብታ ሁሉ፣
15 ረጃጅሙን ግንብ ሁሉ፣የተመሸገውን ቅጥር ሁሉ፣
16 የተርሴስን መርከቦች ሁሉ፣የክብር ጀልባዎችን ሁሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው።
17 የሰው እብሪት ይዋረዳል፤የሰውም ኵራት ይወድቃል፤በዚያን ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል፤
18 ጣዖቶች ሁሉ ፈጽሞ ይወድማሉ።
19 እግዚአብሔር ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፣ሰዎች ከአስፈሪነቱከግርማውም የተነሣ፣ወደ ዐለት ዋሻወደ መሬትም ጒድጓድ ለመሸሸግ ይሮጣሉ።
20 በዚያን ቀን ሰዎችሊያመልኳቸው ያበጇቸውን፣የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውንለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይወረውራሉ።
21 እግዚአብሔር ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፣ሰዎች ከአስፈሪነቱእንዲሁም ከግርማው የተነሣ፣ወደ ድንጋይ ዋሻ፣ወደ ዐለት ስንጣቂ ሮጠው ይገባሉ።
22 እስትንፋስ አፍንጫው ላይ ባለችበሰው አትታመኑ፤ከቶ ምን የሚበጅ ነገር አለው!