ኢሳይያስ 18 NASV

በኢትዮጵያ ላይ የተነገረ ትንቢት

1 በኢትዮጵያ ወንዞች ዳር ለምትገኝ፣ፉር ፉር የሚሉ ክንፎች ላሉባት ምድር ወዮላት!

2 ይህችውም መልእክተኞችን በባሕር፣ከወንዞች ማዶ በደንገል ጀልባ የምትልክ ናት።እናንት ፈጣን መልእክተኞች፤ረጃጅምና ቈዳው ወደ ለሰለሰ፣ከቅርብም ከሩቅም ወደሚፈራ ሕዝብ፣ኀያልና ቋንቋው ወደማይገባ፣ወንዞች ምድሩን ወደሚከፍሉት መንግሥት፣ ሂዱ!

3 እናንት የዓለም ሕዝቦች፣በምድርም የምትኖሩ ሁሉ፣በተራሮች ላይ ምልክት ሲሰቀል ታዩታላችሁ፤መለከትም ሲነፋ ትሰሙታላችሁ።

4 እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛል፤“ጸጥ ብዬ እቀመጣለሁ፤ከማደሪያዬም በፀሓይ ሐሩር እንደሚያ ብረቀርቅ ትኵሳት፣በመከርም ሙቀት እንደ ደመና ጠል ሆኜ እመለከታለሁ።”

5 ከመከር በፊት የአበባው ወቅት ሲያልፍ፣አበባው የጐመራ የወይን ፍሬ ሲሆን፣የወይን ሐረጉን ተቀጥላ በመግረዣ ይገርዘዋል፤የተንሰራፋውንም ቅርንጫፍ ቈራርጦ ያስወግደዋልና።

6 ሁሉም በተራራ ላይ ለሚኖሩ ነጣቂ አሞሮችለዱርም አራዊት ይተዋሉ፤አሞሮች በጋውን ሁሉ ሲበሉት ይባጃሉ፤የዱር አራዊትም ክረምቱን ሁሉ ሲበሉት ይከርማሉ።

7 በዚያን ጊዜ ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር፣ረጃጅምና ቈዳው ከለሰለሰ፣ከቅርብም ከሩቅም ከሚፈራ ሕዝብ፣ኀያልና ቋንቋው ከማይገባ፣ወንዞችም ምድሩን ከሚከፍሉት መንግሥት፣ገጸ በረከት ይመጣለታል፤ ገጸ በረከቱም የሚመጣለት የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስም ወዳለበት ወደ ጽዮን ተራራ ነው።

ምዕራፎች

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26 27 28 29 30 31 32 33 34 35 36 37 38 39 40 41 42 43 44 45 46 47 48 49 50 51 52 53 54 55 56 57 58 59 60 61 62 63 64 65 66