ኢሳይያስ 20 NASV

በግብፅና በኢትዮጵያ ላይ የተነገረ ትንቢት

1 ዋናው የጦር አዛዥ በአሦር ንጉሥ በሳርጎን ተልኮ፣ የአዛጦንን ከተማ ወሮ በያዘበት ዓመት፣

2 በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር የአሞጽን ልጅ ኢሳይያስን፣ “ማቁን ከሰውነትህ፣ ጫማህን ከእግርህ አውልቅ” ሲል ተናገረው። እርሱም እንዲሁ አደረገ፤ ዕርቃኑንና ባዶ እግሩን ተመላለሰ።

3 ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ባሪያዬ ኢሳይያስ ሦስት ዓመት በግብፅና በኢትዮጵያ ለምልክትና ለማስጠንቀቂያ ዕርቃኑንና ባዶ እግሩን እንደሄደ፣

4 እንዲሁ የአሦር ንጉሥ ወጣትና ሽማግሌ የሆኑትን የተማረኩ ግብፃውያንንና የተሰደዱ ኢትዮጵያውያንን ዕርቃናቸውንና ባዶ እግራቸውን ይወስዳቸዋል፤ መቀመጫቸውን ገልቦ በመስደድም ግብፅን ያዋርዳል።

5 በኢትዮጵያ ተስፋ ያደረጉ፣ በግብፅ የተመኩ ይፈራሉ፤ ይዋረዳሉም።

6 በዚያ ቀን በዚህ ባሕር ዳርቻ የሚኖረው ሕዝብ፣ ‘የተመካንባቸው፣ ከአሦር ንጉሥ ለማምለጥና ነጻ ለመውጣት የተሸሸግንባቸው ምን እንደ ደረሰባቸው ተመልከቱ እንግዲህ እኛስ እንዴት እናመልጣለን?’ ይላል።”

ምዕራፎች

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26 27 28 29 30 31 32 33 34 35 36 37 38 39 40 41 42 43 44 45 46 47 48 49 50 51 52 53 54 55 56 57 58 59 60 61 62 63 64 65 66