ኢሳይያስ 15 NASV

በሞዓብ ላይ የተነገረ ትንቢት

1 ስለ ሞዓብ የተነገረው ንግር ይህ ነው፤የሞዓብ ዔር ፈራረሰች፤በአንድ ሌሊትም ተደመሰሰች።የሞዓብ ቂር ፈራረሰች፣በአንድ ሌሊት ተደመሰሰች።

2 ዲቦን ወደ መቅደሱ ወጣ፤ሊያለቅስም ወደ ኰረብታው ሄደ፤ሞዓብ ስለ ናባው፣ ስለ ሜድባም ዋይታ ያሰማል፤ራስ ሁሉ ተመድምዶአል፤ጢምም ሁሉ ተላጭቶአል።

3 በየመንገዱም ማቅ ይለብሳሉ፤በየሰገነቱና በየአደባባዩሁሉም ያለቅሳሉ፤እንባም ይራጫሉ።

4 ሐሴቦንና ኤልያሊ ጮኹ፤ድምፃቸው እስከ ያሀድ ድረስ ተሰማ፤ስለዚህ የሞዓብ ጦረኞች ጮኹ፤ልባቸውም ራደ።

5 ልቤ ስለ ሞዓብ አለቀሰ፤ስደተኞቿም እስከ ዞዓር፣እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ሸሹ፤እንባቸውን እያፈሰሱወደ ሉሒት ወጡ፤በሖሮናይም መንገድም፣ስለ ጥፋታቸው ዋይ እያሉ ነጐዱ።

6 የኔምሬ ውሆች ደርቀዋል፤ሣሩ ጠውልጎአል፤ቡቃያውም ጠፍቶአል፤ለምለም ነገር አይታይም።

7 ስለዚህ ያገኙትን ሀብት፣ያከማቹትን ንብረት ከአኻያ ወንዝ ማዶ ተሸክመው ያሻግሩታል።

8 ጩኸታቸው እስከ ሞዓብ ዳርቻ ድረስ ያስተጋባል፤ዋይታቸው እስከ ኤግላይም፣ሰቈቃቸውም እስከ ብኤርኢሊም ደረሰ።

ምዕራፎች

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26 27 28 29 30 31 32 33 34 35 36 37 38 39 40 41 42 43 44 45 46 47 48 49 50 51 52 53 54 55 56 57 58 59 60 61 62 63 64 65 66