6 ሆኖም የወይራ ዛፍ ሲመታ፣ሁለት ወይም ሦስት ፍሬ በቅርንጫፍ ራስ ላይ እንደሚቀር፣አራት ወይም አምስት ፍሬም ችፍግ ባለው ቅርንጫፍ ላይ እንደሚቀር፣እንዲሁ ጥቂት ቃርሚያ ይተርፋል”ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር።
7 በዚያ ቀን ሰዎች ወደ ፈጣሪያቸው ይመለከታሉ፤ዐይኖቻቸውም ወደ እስራኤል ቅዱስ ያያሉ።
8 በእጃቸውም ወደ ሠሯቸው መሠዊያዎች አይመለከቱም፤በጣቶቻቸው ላበጇቸው የዕጣን መሠዊያዎች፣ለአሼራም የአምልኮ ዐምዶችክብር አይሰጡም።
9 በዚያን ቀን በእስራኤል ልጆች ምክንያት የተተውት ጠንካራ ከተሞች ጥሻና ውድማ እንደሆኑ ሁሉ፣ እነዚህ ሁሉ ባድማ ሆናሉ።
10 አዳኝ አምላክህን ረስተሃል፤መሸሸጊያ ዐለትህንም አላስታወስህም፤ስለዚህ ምርጥ ተክል ብትተክልም፣እንግዳ ዘርንም ብትዘራ፣
11 በተከልህበት ቀን እንዲበቅል፣በዘራህበትም ማግሥት እንዲያብብ ብታደርግ እንኳ፣መከሩ በደዌና በማይሽር ሕመም ቀን፣እንዳልነበረ ይሆናል።
12 አቤት፤ የብዙ ሕዝቦች የቍጣ ድምፅእንደ ባሕር ሞገድ ይጮኻል፤አቤት፤ የሰዎች ከፍተኛ ጩኸት!እንደ ኀይለኛ ውሃ ያስገመግማል።