1 ዳዊት የሰፈረብሽ ከተማ፣አርኤል፣ አርኤል ወዮልዓመት በዓመት ላይ ጨምሪ፣ዐውደ ዓመትሽም ይቀጥል።
2 ነገር ግን አርኤልን እከባለሁ፤ታለቅሳለች፤ ዋይ ዋይ ትላለች፤ለእኔም እንደ መሠዊያ ስፍራ ትሆንልኛለች።
3 በዙሪያሽ እሰፍራለሁ፤በቅጥር እከብሻለሁ፤የከበባ ዐምባም ሠርቼ አስጨንቅሻለሁ።
4 ወደ ታች ትወርጃለሽ፤ ከምድርም በታች ትናገሪያለሽ፤ንግግርሽ ከትቢያ እየተጒተመተመ ይወጣል፤ድምፅሽ እንደ መናፍስት ድምፅ ከመሬት ወደ ላይ ይመጣል፤ንግግርሽ ከትቢያ ያንሾካሹካል።